Fana: At a Speed of Life!

ወደ ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የሚገቡ አልሚ ድርጅቶች ወደ ትግባራ እንዲገቡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የሚቋቋመው የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና አልሚዎች የጀመሩትን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መሸጋገር እንዳለባቸው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ በድሬዳዋ በሚቋቋመው ነፃ የንግድ ቀጠና ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ላይ አቶ ደንጌ ቦሩ እንደገለጹት÷ አዲስ የሚቋቋመው የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና አልሚ ድርጅቶች የሆኑት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ድርጅት ድርሻቸውን መሠረት ባደረገ መልኩ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ትግባራ መግባት አለባቸው፡፡

አልሚዎች በቂ ፋይናንስና የሰው ኃይል በማሰማራት ለምስረታው እውን መሆን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በነፃ የንግድ ቀጠናው ለመጋዘንነትና ለኤክስፖርት ማቀነባበሪያነት የሚያገለግሉ ሼዶች ዝግጁ መሆናቸው፣ በቀጠናው ውስጥ የድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እና የኢንዱስትሪ ፓርኩ ከድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ጋር የሚያገናኘው መንገድ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑና ለቀጠናው ስራ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች መሟላታቸው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.