Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ።

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ የ2014 በጀት ዓመት በፈተናዎች የተሞላ ቢሆንም ሕዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ልማቱን አስቀጥሏል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላም እንዳይኖራት ለማድረግ የማይተኙ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሕዝቡን በብሔርና በሃይማኖት በማጋጨት ለማተራመስ ቢሞክሩም÷ በመንግስትና በሕዝቡ ብርቱ ትግል መክሸፉን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው የሸኔ ቡድን በወለጋ በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ምክር ቤቱ በፅኑ ማውገዙንም ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ በደራሼ ልዩ ወረዳ በሕዝብ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሲያደርስ መቆየቱን ጠቁመው÷ ቡድኑን ለመደምሰስ መንግስት የጀመረውን የተጠናከረ ዘመቻ በመደገፍ ትግሉ ከግብ እንዲደርስ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

ከፈተናዎቹ ባሻገር የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውንም አፈ-ጉባዔዋ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ በሦስት ቀናት ቆይታው የክልሉን መስተዳድር ምክር ቤት የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አደማጦ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የክልሉን መንግስት በጀት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የ2015 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንደሚጸድቅና ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡

በቢቂላ ቱፋ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.