Fana: At a Speed of Life!

ዘጠኝ ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሦስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ወደ ኢትዮጵያ ተላከ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ በተከሰተው የፋብሪካዎች መዘጋት ምክያት ተጓቶ የነበረው ሦስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን መገጣጠም ተጠናቆ በቂ ፍተሻ ከተደረገበት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል፡፡
በኢትዮጵያ መርከቦች ድርጅት ትብብር መሰረት በመርከብ ወደ ጂቡቲ ወደብ ጉዞ የጀመረ ሲሆን÷ በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ማሽኑ ለአማራ ክልል መንግስት የጣና እና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በነጻ የተበረከተ ነው፡፡
ማሽኑ ሦስተኛ ማሽን ሲሆን÷ ከዚህ ቀደም ሁለት የእንቦጭ ማጨጃ ማሽኖች ለክልሉ መለገሳቸው ይታወሳል፡፡
በአጠቃላይ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ወይም 172 ሺህ 970 ዶላር ወጪ የተደረገበት ይህ ባለ 80 የፈረስ ጉልበት የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን በአንድ ጊዜ 27 ነጥብ 5 ኪዩቢክ ሜትር መያዝ ይችላል፡፡
ማሽኑ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ ለማስወገድ በሚደረገው ርብርብ ላቅ ያለ ግልጋሎት ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡
ወጪው የተሸፈነው ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ፣ በዳላስ፣ በችካጎ እና በእንግሊዝ በተደረጉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ ገንዘባቸውን በለገሱ ኢትዮጵያውያን ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.