Fana: At a Speed of Life!

ጆ ባይደን የዓየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መደቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዓየር ንብረት ለውጥን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቋቋም የሚያስችል መሠረተ ልማት ለመገንባት 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መድበዋል፡፡

ባይደን በዓየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየጨመረ የመጣው ከባድ ሙቀት አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ታውቋል።

ከ20 በላይ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ በአሥር ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሙቀቱ ተጽዕኖ ያሰጋቸዋል ነው የተባለው፡፡

የአሜሪካ መንግስት ይፋ ያደረገው ገንዘብ የጎርፍ አደጋ ሥጋቶችን ለመቆጣጠር ፣ ኅንጻዎችን ለማደስ እና በኅንጻዎቹ ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች ቤቶቻቸውን ማሞቅ እና ማቀዝቀዝ ይችሉ ዘንድ የኃይል ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን የሚውል እንደሆነም ተነግሯል።

በሜክሲኮ ባሕረ ሠላጤ አካባቢ ለሚኖሩ ሠራተኞችም ከንፋስ እና ከሌሎች የኃይል አማራጮች ልማት ተጠቃሚ መሆን የሚችሉበትን አማራጮች እንደሚፈልግ እና ድጋፍ እንደሚያደርግ የባይደን አስተዳደር ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.