Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአፋር ክልል የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍል የቤት መስሪያ የሚሆን የ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል ።

እንዲሁም የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የብድሩ ፋውንዴሽን እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል አመራሮች በሠመራ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የአረንጓዴ አሻራ ማሳረፋቸውን የአፋር ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.