Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ወደ ጀርመን ጋዝ የምታስተላልፍበትን ኖርድ ስትሪም አንድ ዳግም ሥራ አስጀመረች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋዝፕሮም በኖርድ ስትሪም አንድ ወደ ጀርመን የሚልከውን የጋዝ አቅርቦት ዳግም ሥራ አስጀመረ።
ሩሲያ ካለፈው ወር ጀምሮ በኖርድ ስትሪም አንድ በኩል ወደ ጀርመን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የምታቀርበውን ጋዝ ከጥገና ጋር በተያያዘ ሟቋረጧ ይታወሳል።
የጋዝ ፕሮም ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት÷ ከዛሬ ጀምሮ መስመሩ ዳግም ጋዝ አቅርቦት መጀመሩን ገልጸው መስመሩ 40 በመቶ የጋዝ ምርት ወደ ጀርመን መላክ ጀምሯል ብለዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራቱ የጋዝ ፍጆታቸውን በ15 በመቶ እንዲቀንሱ መጠየቁን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.