Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በመጪው ማክሰኞ አዲስ አበባ ይገባሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በመጪው ማክሰኞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡
ሰርጌ ላቭሮቭ በአዲስ አበባ የሁለት ቀናት ቆይታ እንደሚኖራቸው ታውቋል።
በቆይታቸውም ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እና ከተለያዩ ሀገራት የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል፡፡
ላቭሮቭ ከአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ጋር በሚያደርጉት ውይይት በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካካል ያለውን ግንኙነት እና ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ባለፈም በሁለተኛው የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ እንደሚመክሩም ኤምባሲው አስታውቋል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.