Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሶስት ውድድሮች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ንጋት 11 ሰአት ላይ ይካሄዳል፡፡
በ800 ሜትር የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ቶሎሳ ቦደና ይሳተፋል፡፡
ሌሊት 10 ሰዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው የ5 ሺህ የማጣሪያ ውድድር÷ አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ አትሌት ጥላሁን ኃይሌ እንዲሁም አትሌት ሙክታር እድሪስ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
ከሌሊቱ 9:10 በሚካሄደው የ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ደግሞ አትሌት ደርቤ ወልተጂ ፣ አትሌት ሃብታም አለሙ እና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ይወዳደራሉ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.