Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት በይፋ ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ ከተማ የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት በይፋ ሥራ ጀምሯል፡፡

የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ ሐሩሳ ÷ሀዋሳ ለኑሮ ተስማሚ፣ ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቱሪዝም ምቹ መሆኗን ጠቅሰው÷ካሏት ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች መካከል አንዱ የሐዋሳ ከተማ ሐይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የባህር ትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩም ለሚመጡ ጎብኚዎች ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

የሐዋሳ ከተማ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለ÷የባህር ትራንስፖርት አገልግሎትን በማዘመን የሐዋሳ ከተማ የቱሪዝም መዳረሻነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የጀልባ ማህበሩ ዋና አስተባባሪ አቶ በሐይሉ ሰለሞን በበኩላቸው÷ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ጀልባ በማህበሩ አባል በመስራት የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል ማለታቸውን ከሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.