Fana: At a Speed of Life!

በ2014 በጀት ዓመት 2 ሺህ 761 አዳዲስ የማምረቻ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎችን ማቋቋም መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው 2014 በጀት ዓመት 2 ሺህ 761 አዳዲስ የማምረቻ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎችን ማቋቋም መቻሉን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2014 እቅድ አፈጻጸሙን የተቋሙ የክልል እና የፌደራል አመራሮቾ እንዲሁም የልማት ባንክ እና ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት እየገመገመ ነው።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማበራከት የሀገር ውስጥ ምርትን ለማስፋፋት እና የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በ2014 በጀት ዓመት 2 ሺህ 761 አዳዲስ የመካካለኛ እና አነስተኛ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ማቋቋም መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም 148 ሺህ 494 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።

በበጀት ዓመቱ 2 ሺህ 374 ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ወደ አነስተኛ ኢንዱስትሪ፣ 479 አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ መካከለኛ እና 53 መካካለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ መሸጋገራቸውን አስረድተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪዎቹ ተመርተው ለውጪ ገበያ ከቀረቡ ምርቶችም 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል።

በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ዘንድ ያለውን የካፒታል እጥረት ለመቅረፍም በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

በበጀት ዓመቱ በክልሎች ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ለስራ ማስኬጃ 1 ቢሊየን 474 ሚሊየን 770 ሺህ 487 ብር ብድር መሠራጨቱ ተመላክቷል።

በመላኩ ገድፍ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.