Fana: At a Speed of Life!

የመንገድ ዘርፉ የሚመራበትን ግልፅ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ ዘርፉ የሚመራበትን ግልፅ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው ረቂቅ የመንገድ ፖሊሲ እና አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ፥ እየተዘጋጀ ያለው ፖሊሲ ከመንገድ ዘርፍ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ይፈታል፡፡
በዘርፉ ያሉ ውስብስብ ችግሮች የመንገድ ጥያቄ፣ የተፈጠረውን ኃብት በአግባቡ የመጠበቅ፣ የአገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች አቅም በሚፈለገው መልኩ ያለማደግ፣ የወሰን ማስከበር ችግሮች፣ የግብዓት ችግሮችና ሌሎችንም ለመፍታት ፖሊሲው ያግዛል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመንገድ ፖሊሲና አዋጅ ባለመኖሩ የመንገድ ዘርፉን በአግባቡ ለመጠቀምና ለመምራት እንዳልተቻለ ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመንገድ አውታር በ1989 ዓ.ም ከነበረበት 26 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር አሁን ከ160 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.