Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዩቤልዩ የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ዘመናዊ ፖሊስ የመገንባት ኃላፊነትቱን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በጀግንነት መጠበቅ፣ በሰብዓዊነት ማገልገል የሚል መሪ ሃሳብን በማንገብ ለፖሊስ ሰራዊት ዕድገትና መሻሻል አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ እንደገለጹት÷ የዩኒቨርሲቲው የቅበላ አቅም ቀድሞ ከነበረው 150 ሰልጣኝ አሁን ወደ 3 ሺህ ማደጉን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.