Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ46 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ የቀረበውን የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ46 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ የቀረበውን የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት አጸደቀ፡፡

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ 46 ቢሊየን 316 ሚሊየን 524 ሺ 693 ብር በጀትን አፅድቋል፡፡

የፀደቀው በጀት ፍትሃዊ በሆነ መልክ ተከፋፍሎ የክልሉን ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማቶችን ለማስቀጠል ስራ ላይ ይዉላል ተብሏል።

በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የክልሉ መንግስት ስራዎችና አገልግሎቶች ወጪ የሚሆነው በጀት ከፌዴራል መንግስትና የክልሉ መንግሥት ከሚያገኘው ገቢ እንደሚሸፈን ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በጀት ውስጥ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ለክልል ማዕከል መስሪያ ቤቶች፣ 37 ነጥብ 4 ቢሊየን ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች፣ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እንዲሁም 3 ቢሊየን ለክልላዊ ፕሮግራሞች እና 2 መቶ ሚሊየኑ ደግሞ ለክልሉ መጠባበቂያ የሚውል ይሆናል ነው የተባለው።

በቢቂላ ቱፋ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.