Fana: At a Speed of Life!

የመማር ማስተማር ተግባራትን በቴክኖሎጂ መደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የመማር ማስተማር ስራ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማኒስቴርና በአሜሪካው የግል ኩባንያ ሲቪሊ መካከል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ እና የሲቪሊ ኩባንያ ጄነራል ማኔጀር ሚስ ረሺዳ ሐዲሽ ፈርመውታል።

ስምምነቱ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ በመጀመር የሚተገበር ሲሆን ፥ የሚገኙ ውጤቶችን በመቀመር ወደ ክልሎች ለማስፋት ያለመ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሲቪሊ የተሰኘው ኩባንያው በአሜሪካ ሀገር የተመዘገበ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ተቋም መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ቴክኖሎጂ የተሟሉላቸው ቨርችዋል ቤተ ሙከራዎችን በትምህርት ቤቶች በመገንባት ለመማር ማስተማር አጋዥ የሆኑ መረጃዎች ለተማሪዎች በቀላሉ እንዲደርሱ የሚሰራ ተቋም ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.