Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች በሐረር ከተማ  ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በሐረር ከተማ ባሕል ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የችግኝተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

ከችግኝ ተከላው ጎን ለጎን የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት የማደስ እና የፅዳት ዘመቻ  ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል የሥራ ከፍተኛ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን  መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.