Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 65 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 65 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት መሄዳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ÷ 65 ሺህ 14 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.