Fana: At a Speed of Life!

በ2014 ዓ.ም በ99 ተቋማት ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ተከስቷል- ኢመደአ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባደረገው የሳይበር ደህንነት ፍተሻና ግምገማ በ99 ተቋማት ላይ የተፈጠረ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትን በመለየት ክፍተቱ እንዲታረም ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በአስተዳደሩ የሳይበር ደህንነት ፍተሻ እና ግምገማ ዲቪዥን ኃላፊ ተወካይ ነጻነት ተካ እንደገለጹት÷ በ2014 ዓ.ም አስተዳደሩ በ99 የመንግስት እና የግል ተቋማት ላይ ባደረገው የደህንነት ፍተሻ ተቋማቱ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ ለሳይበር ጥቃት መጋለጣቸውን አረጋግጧል፡፡
ከተለዩት የሳይበር ደህንነት ክፍተቶች መካከል÷ 28 በመቶ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ፣ 45 በመቶ ያህሉ መካከለኛ እና 27 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳታቸው ዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ላይ መሆናቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የተገኙት ክፍተቶች ባብዛኛው÷ የደህንነት ስታንዳርድን ተከትሎ ያለመስራት፣ ያልታደሱ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ ደካማ የሆነ የዝማኔ መጠገኛ ስርዓቶች እና የአካባባዊ ደህንነት እና ቁጥጥር ስርአቶችን መከተል፣ እንዲሁም ደካማ የሆኑ እና ከአምራች ድርጅት የመጡ የይለፍ ቃል መጠቀም፣ ዳታ በሚዘዋወርበት ወቅት ምስጠራ አለመጠቀም፣ የደህንነት ኮንፊግሬሽኖችን አለማስተካከል መሆናቸውን አብራርተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.