Fana: At a Speed of Life!

በወጪ ንግድ ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ላስገኙ ላኪዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስሰር ሚኒስቴር በ2014 በጀት ዓመት በወጪ ንግድ ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ላስገኙ ላኪዎች ዛሬ እውቅና ሰጠ።

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ቀን “የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ምርት ይግዙ” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት እና እውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ተካሄዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በወጪ ንግድ የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በእውቅና መርሐ ግብሩ በጀት ዓመት በወጪ ንግድ ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ላስገኙ ላኪዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የተሰጠው እውቅና ባለሃብቶች በወጪ ንግድ ላይ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማበረታት እንደሚያገዝ ተገልጿል።

በተያያዘም የወጪ ንግድ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት የበጀት ዓመቱ የወጪ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።

የንግድ ቀኑ መከበር የኢትዮጵያን ምርቶች መለያ ለማድረግ ይጠቅማል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 12 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.