Fana: At a Speed of Life!

ፀሐይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሥራውን በይፋ ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀሐይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በዛሬው ዕለት ሥራውን በይፋ ጀመረ፡፡

በባንኩ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ፥ የባንኩ የቦርድ አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፥ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ አዳዲስ ባንኮች ገበያውን በመቀላቀል ረገድ እየታየ ያለው ለውጥ በማኅበረሰቡ ውስጥ የባንክ ሥራ እውቅና እንዲኖረው ከማድረግ አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በተለይም የገጠሩን ማኅበረሰብ የባንክ ተጠቃሚነት በተቀላጠፈ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ የግል ባንኮች ወደ ገበያው በዚህ መንገድ መግባታቸው ትልቅ ዕድል በመሆኑ በተገቢው መንገድ ተደራሽ መሆን ላይ በትኩረት መሥራት ይገባልም ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ የውጭ ባንኮችም ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን እና ለሀገር ውስጥ ባንኮች ወድድሩ ቀላል ስለማይሆን ጠንክረው መሥራት እንደሚገባቸውም በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

ባንኩ ሥራውን የጀመረው 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል እና 734 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዞ መሆኑም ነው የተገለጸው።

የባንኩ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ መስፍን በበኩላቸው ÷ ባንኩ የመደበኛ የባንክ አገልግሎትና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም የዲጂታል ባንኪንግ ሥራዓት በመዘርጋት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ሥራ መግባት ችሏል ብለዋል።

ፀሐይ ባንክ በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመረው በ30 ቅርንጫፎቹ እንደሆነና በያዝነው በጀት ዓመት የባንኩን ቅርንጫፎች 100 ለማድረስ ዕቅድ ይዙ እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.