Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀከቶች እየተመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 20 የልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው።
ፕሮጀክቶቹ እየተመረቁ ያሉት÷ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ፈትያ አደም ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና የካቢኔ አባላት በተገኙበት ነው።
የውሃ፣ የካይዘን የምርምር ተቋም ግንባታ፣ የቤቶች ልማት ፣የማምረቻ ሼዶች፣ ድልድይ እና የጤና ተቋማት እየተመረቁ ካሉ ፕሮጀክቶች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው።
የአስተዳደሩ የንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዪ ትናንት በሰጡት መግለጫ ፥ በከተማ 10፣ በገጠር 10 የተገነቡት የመሠረተ ልማት ሥራዎች የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡
በተለይም በጤናው ዘርፍ የነዋሪው የዘመናት ጥያቄ የነበረውን ሲቲ ስካን በ40 ሚሊየን ብር በመግዛት ለአገልግሎት ማብቃቱን ጠቁመዋል፡፡
በንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚነት በኩል በከተማ አስተዳደሩ የሚታየውን የመቆራረጥና የንፅህና ችግር ለመፍታት የለገ ኦዳና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተሠርቶ መጠናቀቁም ከፍ ያለ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
የአርሶ አደሩን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያስችል ዘንድም÷ የአሰሊሶ የመስኖ ውሃ ፕሮጀክት ስራ እንደሚጀምር አመላክተዋል።
የልማት ሥራዎቹ በ2014 እና ከዛ ቀደም ባሉ ዓመታት ወደ ግንባታ መግባታቸውን የጠቀሱት ኃላፊው÷ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡
በነገው ዕለትም የገጠሩን ህብረተሰብ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ የመስኖ እና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንደሚመረቁ ተገልጿል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.