Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፈው በጀት ዓመት ከ27 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፈው በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 27 ነጥብ 72 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ መዓዛ አለማየሁ እንደገለፁት÷ ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ 20 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ የተገኘ ነው፡፡

ከአዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ መስመር ማስቀጠያ ደግሞ 6 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር፣ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭና ከልዩ ልዩ ገቢ 113 ሚሊየን ብር መገኘቱን ዳይሬክተሯ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አገልግሎቱ የኤሌክትሪክ ኃይልን በጅምላ ገዝቶ ለደንበኞቹ የሚሸጥ መሆኑን ተከትሎ በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 10 ቢሊየን 563 ሚሊየን 544 ሺህ 247 ብር ለኢትዮያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተከፈለ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.