Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት “የዝንጀሮ ፈንጣጣ” የዓለማችን አሳሳቢ በሽታ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቂት አገሮች በቅርቡ የተከሰተው “የዝንጀሮ ፈንጣጣ” በሽታ የዓለማችን አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑን  የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መሆኑንና ባልተጠበቀ ሁኔታ በዓለማችን በ70 ሀገራት ውስጥ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ነው ያስታወቀው።

በሽታው ክትባት ያልተገኘለትና ለሕክምናውም ከፍተኛ ኢቨስትመንት የሚጠይቅ ሌላኛው የዓለማችን አሳሳቢ ወረርሽኝ ሆኗል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አውጇል።

በመሆኑም የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከአገር ወደ አገር በቀላሉ ሊስፋፋ የሚችል ቀውስ በመሆኑ የበሽታውን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል የተቀናጀ ዓለም አቀፋዊ ምላሽ ያስፈልጋል  ነው የተባለው፡፡

በከኢቦላና ከኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ቀጥሎ የዓለማችን ህዝብ የጤና ቀውስ ተብሎ ሲመዘገብ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሌላኛው አደገኛ ተላላፊ በሽታ መሆኑ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ሽታው የሚተላለፈው “መንኪፖክስ’ በተባለ ቫይረስ አማካይነት ሲሆን፥ ለፈንጣጣ በሽታ ከሚያጋልጠው ቫይረስ ጋር ተዛማጅነት እንዳለው ይነገራል።

ቫይረሱ ሊተላለፍ የሚችለው በበሽታው ከተያዘ ሰው ወይም እንስሳት ጋር የቅርብ ንክኪሲ ሲኖር እንደሆነም ይታመናል።

ቫይረሱ ወደ ስውነታችን የሚገባውም በቆዳችን ክፍተቶች በኩል፣ በዓይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ሊሆን እንድሚችል ነው የጤና ባለሙያዎች የሚገልጹት።

ምንጭ ሲኤን ቢሲና አረቢያኒውስ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.