Fana: At a Speed of Life!

ቱኒዚያውያን አዲስ በተዘጋጀው የሕገ መንግስት ረቂቅ ላይ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱኒዚያውያን በአዲስ መልኩ በተዘጋጀው የሕገ መንግስት ረቂቅ ላይ የሕዝበ ውሳኔ ድምጽ እየሰጡ ነው፡፡
 
ለድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ መከፈታቸው ተመላክቷል፡፡
 
የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ የአገሪቱን መንግስት ካባረሩ እና ፓርላማውን ካገዱ በኋላ ቱኒዚያ በአዋጅ እንድትመራ ከወሰኑ ዛሬ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አስታውሷል፡፡
 
የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ ተከትሎም ስርዓቱን ወደ አንድ ሰው አገዛዝ ለመመለስ የተደረገ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ነው ሲሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሲተቹ ቆይተዋል፡፡
 
ረቂቁ ለፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ የበለጠ ስልጣን ከመስጠቱ ባለፈ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ሚና እንደሚገድብ እና ቅቡልነት እንደሌለውም ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዚዳንት ካይስ ሰኢድ በበኩላቸው÷ በአገሪቱ በሙስና የተዘፈቀ የፖለቲካ ልሂቃንን ለመቆጣጠር ያደረጓቸው ለውጦች አስፈላጊ እንደሆኑ ነው የሚያስረዱት፡፡
 
በህዝበ ውሳኔው ለመሳተፍ 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን÷ በምርጫው ዕለት መራጮች በተሳሳተ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ችግር መፍጠራቸው ተጠቁሟል፡፡
 
አዲሱ ሕገ መንግስት 10 ምዕራፎች እና 142 አንቀጾችን የያዘ እና ቱኒዚያ በፕሬዚዳንታዊ ስርዓት የምትመራ ሉዓላዊ ሀገር መሆኗን የሚደነግግ ነው።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.