Fana: At a Speed of Life!

“ጋሸና የሀገር ዋስትና” በሚል መሪ ቃል በክልሉ ወጣቶችና ሴቶች ሊግ አስተባባሪነት የችግኝ ተከላ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”ጋሸና የሀገር ዋስትና” በሚል መሪቃል በአማራ ክልል ወጣቶችና ሴቶች ሊግ አስተባባሪነት ከመላው የአማራ ክልል አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት በአንድ ጀንበር 50 ሺህ አገር በቀል ችግኝ ለመትከል የተዘጋጀ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተካሄደ።
 
በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ አጤ ውሃ ምሽግ በተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ወጣቱ የተራቆቱ አካባቢዎችን ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ የድርሻችውን ሊወጣ እንደሚገባ ተመላክቷል።
 
ከዚህ ባለፈም ጀግኖች የኢትዮጵያ ኃይሎች የአሸባሪውን ህወሓት ወረራ ድባቅ በመምታት ታሪክ የሰሩበትንና መስዋዕትነት የተከፈለበትን የጋሸና ግንባር በአረንጓዴ ልማት ከመሸፈን ባሻገር በጦርነቱ መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖችን ለማሰብ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
 
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ÷ ወጣቶች በየአካባቢያቸው ራሳቸውን በማደራጀት በጦርነቱ ያሳዩትን አንድነት በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በመሳተፍ የተራቆቱ አካባቢዎችን ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ለዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
 
የክልሉ ወጣቶች በሌሎች ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የድርሻችውን ሊወጡ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡
 
በታሪካዊው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የፌደራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶችና ሴቶች መሳተፋቸውን ከአማራ ክል ደንና አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ያገኘነውመረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.