Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ጋር ተመካክረዋል፡፡

ምክክሩ በግንቦት ወር በጄኔቫ የተካሄደውን ውይይት ተከትሎ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ባለሙያዎቹ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመወጣት ከመንግስት ጋር በጋራ መፍትሄ ለመፈለግ አዲስ አበባ መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ግጭት አውድ ውስጥ የደረሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ ያቋቋመው ዓለም ዓቀፍ የሰብዐዊ መብቶች የባለሙያዎች ኮሚሽን ከአገራችን ጋር የትብብር እድልን አስመልክቶ ውይይት ለማድረግ በአዲስ አበባ ይገኛሉ።

በዝርዘር የእንቅስቃሴ አቅጣጫዎች ማዕቀፍ ላይ መሰማማት ከተቻለ፥ ከኮሚሽኑ ጋር የመተባበርን ጉዳይ መልሶ የማጤን እድልን አስመልክቶ በጄኔቫ የተጀመሩ ውይይቶችን ለመቀጠል የባለሞያዎቹ ኮሚሽን አባላት ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና አግባብነት ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.