Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ ከ250 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደሴ ከተማ አስተዳደር ከ250 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የአስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

ለአገልግሎት የበቁት በደሴ ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ ሲካሄዱ ከቆዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ መሆናቸውን የመምሪያው ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱልከሪም ሀብታሙ ገልጸዋል።

ከፕሮጀክቶችም 1 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የድንጋይ ንጣፍ መንገድ፣ የፒያሳ የእግረኛ ማቋረጫ ድልድይ፣ ሶስት ኪሎ ሜትር አዲስ መንገድ ከፈታ፣ አምስት ኪሎ ሜትር ጠጠር መንገድና 16 ኪሎ ሜትር መንገድ ጥገና ይገኙበታል።

እንዲሁም በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የቢሮ ተቋማት መልሶ ግንባታና ቁሳቁስ ማሟላት ስራዎች መከናወናቸውንም ጠቅሰው፥ ፕሮጀክቶቹ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያግዙ መሆናቸውና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታቸውም የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።

መሰረተ ልማቶቹ አቅም በፈቀደ ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ መደረጉን ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡም የጀመረውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አክለውም በተያዘው የበጀት ዓመትም ከግማሽ ቢሊየን ብር በሚበልጥ በጀት ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ የሮቢት ድልድይ፣ ኮሽን በር-ገራዶ 3 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ለመስራት መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.