Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ክልልን ከካርቦን ሽያጭ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደን ሽፋኑ በሕዝቡ ተጠብቆ የቆየው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከካርቦን ሽያጭ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃ እና አየር ንብረት ጥበቃ ቢሮ ገለጸ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለረዥም ዓመታት የቆየ ደንን የመጠበቅ ባህል ያለው ቢሆንም÷ ከካርበን ሽያጭ ተጠቃሚ እንዲሆን በአግባቡ አልተሠራም ብሏል ቢሮው፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አስራት ገብረ ማርያም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ካለው የቆዳ ስፋት ከ40 ከመቶ በላይ የሚሆነው በደን የተሸፈነ ነው፡፡
ምንም እንኳን ክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው የደን ሽፋን ቢኖረውም ከካርበን ሽያጭ ገቢ እያገኘ አለመሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አሁን ባለው አሠራር የካርበን ክፍያ ሕግ የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው ሲለሙ ብቻ እንደሚከፍል ጠቁመው÷ ይህ ብቻውን መስፈርት መደረጉ ተገቢ አለመሆኑንን ገልጸዋል፡፡
ይህም ደንን ጠብቆ ለትውልድ እያሻገረ ለሚገኝ ማህበረሰብ አበረታች አይደለም ብለዋል።
በቀጣይ “ደንን ጠብቆ ማቆየት የካርበን ክፍያ ማስገኘት አለበት” በሚል ክልሉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመሥራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
በዓለማየሁ መቃሳ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.