Fana: At a Speed of Life!

 “ስለኢትዮጵያ” የፓናል ውይይት እና የፎቶ አውደ ርዕይ በአዳማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 7ኛው “ስለኢትዮጵያ” የተሰኘው የፓናል ውይይት እና የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ “የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በፓናል ውይይቱ እና የፎቶ አውደ ርዕዩ ላይ÷ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አስፋ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጄልዴ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

የፎቶግራፍ አውደ ርዕይዩን ዶክተር ፍፁም አስፋ፣ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ እና አቶ ኃይሉ ጄልዴ ከፍተውታል፡፡

በአውደርዕዩ ላይ ከ1950ዎቹና 60ዎቹ ጀምሮ በየዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ሁነቶች፣ በታሪክ አንጓዎች የተከሰቱ የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲሁም ለአገር ሉዓላዊነት የተከፈሉ መስዋዕትነቶችንና ከኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ጉዞ ጋር ተያያዥነት ያላቸው  አገራዊ ክንውኖችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዕይታ መቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧ፡፡

“ስለኢትዮጵያ”  ከዚህ ቀደም በጅግጅጋ፣ ድሬደዋ፣ ሀረር፣ ሃዋሳ፣ አርባምንጭ እና ጅማ ከተሞች መካሄዱ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.