Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ካቢኔ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ለልዑካን ቡድኑ የተለያዩ ሽልማቶች እንዲሰጥ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደ 18ኛው ዓለም ዐቀፍ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ልዑካን ቡድኑን ለማመስገን የተለያዩ ሽልማቶችን እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል ።

አስተዳደሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ላሳዩት ኢትዮጵያዊ ጀግንነት እና ላስገኙት ውጤት የምስጋና መርሃ ግብር ነገ እንደሚያካሂድ አስታውቋል፡፡

ካቢኔው ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችና ልዑካን ቡድኑን ለማመስገንም የተለያዩ ሽልማቶችን እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል ።

የከተማዋ ነዋሪዎችም ነገ ማለዳ ምስጋናቸውን የሚገልፁበት ደማቅ ስነስርዓት እንደሚካሄድ ከከንቲባ ፅህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.