Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው፡፡
በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ያስመዘገበው ቡድኑ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በዛሬው ዕለትም ሕዝቡ ለጅግኖች አትሌቶቹና ለሌሎች የልዑኩ አባላት በተመረጡ የመዲናዋ አካባቢዎች አቀባበል በማድረግ አድናቆቱን ይገልጻል፡፡
አሁን ላይም የአትሌቲክስ ቡድኑ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል በአጀብ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በደማቅ ሁኔታ ለመጓዝ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.