Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሕንድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሕንድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ÷ በደቡባዊ ሕንድ ከሚገኙ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በደቡባዊ ሕንድ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ተቋማት በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን መስኮች ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ሕንድ ለቡራዩ ልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት በአካል እና በኦንላይን ባለሙያዎችን ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢ ሁኔታ የመፍጠር ሥራን እንደምትደግፍ አረጋግጣለች፡፡
ሀገራቱ በጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና በቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ተቋማት ድጋፍ፣ በባለሙያዎች አቅም ግንባታ እና በሌሎችም የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የትብብር ዘርፎች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.