Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች የምስጋና መርሃ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች የምስጋና መርሃ ግብር አከናወኑ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ክብር ምስጋን ለእርሱ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን ብለን፣ ለአንድ ደቂቃ በያለንበት ቆመን ለኢትዮጵያ አምላክ ምስጋና እንድናቀርብ” ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ይህንን ጥሪ በመቀበልም ነው የተቋሙ ሰራተኞች የምስጋና መርሃ ግብሩን ያከናወኑት።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ባስተላለፉት መልዕክት፥ “እኛ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሰራተኞች ችግር ፈተና አያደናቅፈንም፤ ኢትዮጵያ ስላደረገችልን እናመሰግናለን፤ በቀጣይም ለሀገራችን እድገት፣ ወንድማማችነት እና ህብረት እንሰራለን” ብለዋል።

“ችግርን የምናሸንፍበት ጎዳና ላይ በመሆንም እርስ በርሳችን እየተመሰጋገንን የሀገራችንን ከፍታ እናረጋግጣለንም” ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.