Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳድሩ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የ10 ሚሊየን ብር ሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት አትሌቶች የምስጋናና የሽልማት መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከተማ አስተዳድሩ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት አትሌቶች የ10 ሚሊየን ብር ሽልማት ማበርከቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

የአትሌቲክስ ቡድኑ ዛሬ በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ሲዘዋወር በህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ቀጥሎ በብሄራዊ ቤተ መንግስት በተከናወነ የአቀባበል ስነ ስረዓት፥ ለቡድኑ አባላት የተለያየ መጠን ያለው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.