Fana: At a Speed of Life!

ድሬዳዋ ለበረሃማነትና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኗ ችግኝ መትከልና መንከባከብ የህልውና ጉዳይ ነው – አቶ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ ለበረሃማነትና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኗ ችግኝ መትከልና መንከባከብ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ በንቃት እንዲሳተፍ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ጥሪ አቀረቡ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፣ ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት እና ዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ጋር በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀምረዋል።

በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ በብልፅግና ፓርቲ የሲቪስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ ፥ በጠቅላይ ሚኒስትራችን አነሳሽነት ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማውረስ የአረንጓዴ አሻራ አስጀምረው በቢሊየን የሚቆጠሩ ችግኞች እንዲተከሉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያዊነት የቆየ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴት ማሳያ እንዲሆን የተቸገሩ ወገኖችን ቤት በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በማካሄድ የብዙዎች ህይወት እንዲለወጥ ማድረግ መቻሉንም ጠቅሰዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በበኩላቸው ፥ በአራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 2 ሚሊየን ችግኞች መዘጋጀታቸውንና 1 ነጥብ 8 ሚሊየኑ በአስተዳደሩ፣ በከተማና በገጠር እንደሚተከሉ የተቀሩት 2ዐዐ ሺህ ችግኞች ለጂቡቲ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ድሬዳዋ ለበረሃማነትና ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኗ ችግኝ መትከልና መንከባከብ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በድሬዳዋ ከተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ እና የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ባሻገር ለ1 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በተሾመ ሃይሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.