Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በአደጋ ስጋት ተጋላጭነት ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014(ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል በአደጋ ስጋት ተጋላጭነት ዙሪያ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት ሰብሳቢ ርስቱ ይርዳ ከበልግ ዝናብ መዘግየት እና መቆራረጥ ጋር ተያይዞ በክልሉ የምርት መቀነስ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ድጋፍ እንደሚፈልጉና ከ700 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልጋቸው በጥናት መለየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል፡፡

የክልሉ መንግሥትም ዜጎችን የመደገፍ ስራ ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ችግሩ በክልሉ አቅም ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ  የፌዴራል መንግሥትና አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚያቀምጥ መገለጹን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.