Fana: At a Speed of Life!

የለገዳዲና የድሬ ግድብን እድሳትና ማሻሻያ ለማከናወን የሚያስችል የ11 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነባሩን የለገዳዲና ድሬ ግድብን እድሳትና ማሻሻያ ለማከናወን ከዊ ቢውልድ (ሳሊኒ) ከተባለ የጣሊያን ኩባንያ ጋር የ11 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ትርፍ ውሃ ማፍሰሻ በሮች፣ የአደጋ ጊዜ ውሃ መቆጣጠሪያና ከግድብ ወደ ማጣሪያ ጣቢያ ውሃ ማውረጃ ጥገና እና ማሻሻያ ስራ እንዲሁም የድሬ ግድብ ደለል ማስወገጃ ጥገና እና ማሻሻያ፣ ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ፥ የከተማችንን የውሃ አቅርቦት ለማሳደግ አዳዲስ የውሃ ፕሮጀክቱችን መገንባትን ጨምሮ የነበሩንን የውሃ ፕሮጀክቶች በቂና ተመጣጣኝ አገልግሎት ለከተማችን ነዋሪዎች መስጠት እንዲችሉ ለማስቻል የጥገናና የማሻሻያ ሥራ በስፋት እያከናወንን እንገኛለን፡፡

የድሬና የለገዳዲ የውሃ ማጠራቀሚያ ግድቦች ካለ በቂ ጥገና 50 ዓመት አገልግለውናል ያሉት ከንቲባዋ ፥ በተጨማሪም ከ50 ዓመት ላለፈ ጊዜ እንዲያገለግሉን የጥገና የዲዛይን ማሻሻያ ሥራው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.