Fana: At a Speed of Life!

በግብርና ሚኒስቴር የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012  (ኤፍ ቢ ሲ)በግብርና ሚኒስቴር የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን ትግበራ መርሃ ግብር ይፋ ተደረጓል።

መርሃ ግብሩ “ካይዘን ለተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ  መሆኑን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በትግበራ እወጃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገልጋይን ፍላጎት በሚያሟላ ሁኔታ የካይዘን ፍልስፍናን በመከተል ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ የግብርና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ካይዘን ኢንስቲትዩት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ ከጥር 2012 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ድረስ ለሚተገበረው የመጀመሪያ ደረጃ የካይዘን የአመራር ፍልስፍና ስልጠና እና ቀጣይነት ያለው ትግበራን ትኩረት ያደረገ የጋራ ስምምነት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከተጀመረ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የካይዘን ፍልስፍና ብክነትን መከላከል ዋና አላማው አድርጎ የተመሰረተ ነው፡፡

የግብርና ሚኒስቴርም የተጣለበትን ሃገራዊ ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ እንዲሁም አርሶና አርብቶ አደሩን የላቀ ቴክኖሎጂን በስፋት እንዲጠቀም ለማስቻል በፋይናንስ፣ በሰው ሃይልና በንብረት ላይ የሚያጋጥሙ ብክነቶችን በመቅረፍና በአግባቡ በመጠቀም ወደ ላቀ ተቋማዊ ለውጥ መድረስ እንደሚገባ በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.