Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ታቦር ከተማ ወደ ሪጂዮፖሊታንት ከተማነት ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ታቦር ከተማ ወደ ሪጂዮፖሊታንት ከተማነት ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

በስነ ስርዓቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ የምክር ቤት አባላት የሃይማኖት አባቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የምትገኘው ደብረ ታቦር ከተማ በ1327 ዓ.ም በዓፄ ሰይፈ አርዕድእዘ እንደተቆረቆረች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከተማዋ ታሪካዊ እና ዕድሜ ጠገብ ከመሆኗ በተጨማሪ የበርካታ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ሰው ሰራሽ መስህቦች መገኛም ናት።

በአሁኑ ሰዓት የአማራ ክልል ምክር ቤት ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከተማዋ ወደ ሪጂዮፖሊታንት ከተማነት እንድታድግ በወሰነው መሰረት የሪጂዮፖሊታንት ከተማ ደረጃን ይዛ ትገኛለች።

በህልውና ዘመቻው ለሀገራቸው ለተዋደቁና ጀብዱ ለፈፀሙ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም በዛሬው ዕለት የደብረታቦር ከተማ ሽልማት ሰጥቷል።

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል ጌታቸው ጉዲናን ጨምሮ በዕዙ ስር የሚገኙ የኮር እና የክፍለ ጦር አዛዦች እንዲሁም በዘመቻው ለተሰዉ የክፍለ ጦር አዛዦች የ200 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቦታ ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተቀበሉ ሲሆን ፥ በጠላት ወረራ ወቅት ደብረታቦር ከተማ እንዳትደፈር ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከከተማዋ ህዝብ የተበረከተ መሆኑ ተጠቅሷል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.