Fana: At a Speed of Life!

ምስጋና – ከጎደሉን ነገሮች ይልቅ ያገኘናቸውን መልካም ስጦታዎች የምንመለከትበት በጎ ተግባር ነው- የካቶሊክ እምነት ተከታዮች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ምስጋና ከጎደሉን ነገሮች ይልቅ ያገኘናቸውን መልካም ስጦታዎች እንድንመለከት የሚያደርግ በጎ ተግባር መሆኑን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ተናገሩ፡፡

የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በልደታ ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ”ኢትዮጵያ ታመስግን” መርሐ ግብርን በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡

መርሐ ግብሩ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በጸሎት እና በሃይማኖታዊ ትምህርቶች ነው የተከናወነው፡፡

በልደታ ማርያም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቆሞስ አባ ታምራት ጡምደዶ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “የሰው ልጅ አመስጋኝ ከሆነ በሕይወቱ ከጎደሉት ነገሮች ይልቅ በምድር ላይ የተሰጡትን መልካም ስጦታዎች ማየት ይችላል” ብለዋል፡፡

በመሆኑም በሕይወታችን ለተደረጉልን መልካም ነገሮች ሁሉ ፈጣሪያችንን ማመስገን አለብን ነው ያሉት።

የልደታ ማርያም ቁምስና ምዕምን አቶ ገብሩ ኃብተዮሐንስ በበኩላቸው፥ የሰው ልጅ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪውን ሊያመሰግን ይገባል ብለዋል፡፡

ሰዎች በዚህ ምድር ለተፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ ሲስተር ዝምታወርቅ መላኩ ናቸው፡፡

ምስጋና በሁኔታዎች ሊገደብ እንደማይገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የእምነቱ ተከታይ የሆኑት አቶ ሚካኤል ኤጃሞ ፥ ፈጣሪን ከማመስገን ባሻገር እርስ በርስ የመደጋገፍና የመመሰጋገን ባህል ሊጎለብት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ሲስተር ዝምታወርቅ መላኩ ፥ በስነ-ምግባር የታነጸና አመስጋኝ ትውልድ ለመገንባት ወላጆች በተገቢው መልኩ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.