Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ ብሌን ግርማቸው በድንገት ሕይወቷ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 ላይ በጋዜጠኝነት ስትሰራ የነበረችው ወይዘሮ ብሌን ግርማቸው በዛሬው ዕለት በድንገት ሕይወቷ አልፏል፡፡

ወይዘሮ ብሌን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወቷ እስካለፈበት ቀን ድረስ በነቀምቴ ፋና ኤፍ ኤም 96 ነጥብ 1 ላይ በጋዜጠኝነት ስታገለግል ቆይታለች።

ወይዘሮ ብሌን ወደ ጋዜጠኝነቱ ዓለም ከመግባቷ በፊት በመምህርነት አገልግላለች።

ወይዘሮ ብሌን ነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለድንገተኛ ሕክምና ገብታ ብትረዳም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም።

ጋዜጠኛ ብሌን ግርማቸው ባለትዳር እና የአንድ ልጅ እናት ነበረች፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጋዜጠኛ ብሌን ግርማቸው ኅልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ÷ ለቤተሰቦቿ አና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ይመኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.