Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የሁሉም ርብርብና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል- አቶ ጃንጥራር አባይ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመዲናዋን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የሁሉም ርብርብና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የስራ እድል ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅህፈት ቤት የ1ኛ ምዕራፍ የ3ኛ ዙር 5 ሺህ 938 የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ በበጀት አመቱ የላቀ አፈፃፀም ላመጡ ወረዳዎችና ባለሙያዎችም እውቅና ሰጥቷል።

አቶ ጃንጥራር አባይ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷መድረኩ ለሚቀጥለው በጀት አመት የስራ ትጋት ስንቅ እንደሚሆን ጠቅሰው÷ በከተማው የስራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚሰራው ስራ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግስት ብቻውን ስራ ፈጣሪ መሆን ባለመቻሉ የግሉ ዘርፍ ሊበረታታና ሊደገፍ እንደሚገባ ነው ያመለከቱት፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል ረዲ በበኩላቸው፥ ተመራቂዎችም ሆነ አምራቾች የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ለማቃለል ከፍተኛ ሚና ያላቸው እንደመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.