Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ ቀንና ሌሊት ላይ በሚካሄዱ የዓለም ሻምፒዮና የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ሦስተኛ ቀኑን በያዘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ቀን እና ሌሊት ላይ በሚካሄዱ የማጣሪያና የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡

ከቀኑ 11 ሰዓት በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር÷ መልኬነህ አዘዘው እና አብዲሳ ፈይሳ ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡

በደቂቃዎ ች ልዩነት 11 ሰዓት 35 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ማጣሪያ÷ ሳሙኤል ፍሬው እና ሳሙኤል ጉዲና ይሳተፋሉ፡፡

በሌላ መርሐ ግብር ደግሞ ሌሊት 7 ሰዓት ከ55 ላይ የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር÷  ኤርሚያስ ግርማ እና አድሃና ካሳዬ ኢትዮጵያን እንደሚወክሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም ሌሊት 8 ሰዓት ከ10 ላይ በሚደረገው የሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር÷ ቅሳነት ዓለም ትሳተፋለች፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.