Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ስርዓቱን ውጤታማ አድርጎ ለመምራት የሥራ ባህል ለውጥ  እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ስርዓቱን ውጤታማ አድርጎ ለመምራት የሥራ ባህል ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2015 ዓ.ም የቅድመ ዝግጅት ሥራ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

ዶክተር ይልቃል ከፋለ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ የአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከተቀለበሰ በኋላ የትምህርት ተቋማትን ወደ ሥራ ለማስገባት የተከናወነው ተግባር በበርካታ ፈተናዎች የተሞላ ነበር ብለዋል፡፡

በየዓመቱ በሚሰጡ ክልላዊና ሀገራዊ የትምህርት ፈተናዎች ክልሉ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመው÷ ካለፈው ዓመት ውጤት ተምረን የተሻለ የትምህርት ሥርዓት ለመገንባትና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መሰማራት ይጠበቅብናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

“ትምህርት ሀገር የሚገነባ ትልቅ መሳሪያ ነው” ያሉት ዶክተር ይልቃል÷ የተሻሻለው የትምህርት ስርዓት በሙከራ ትግበራው የተሻለ አሠራሮችን ይዞ የመጣና በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሰጡት ግብዓት ተጨምሮበት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ በበኩላቸው÷ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም  በክልሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.