Fana: At a Speed of Life!

በትምህርት የታነጸ አና በእውቀት የተገነባ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርት ስርዓቱን በቅንጅት መምራት ይጠይቃል-ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በትምህርት የታነጸ አና በእውቀት የተገነባ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርት ስርዓቱን በቅንጅት መምራት ይጠይቃል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ጋሽ ዋጌሾ ገለጹ፡፡
የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም፣ የ2015መሪ ዕቅድና የ2015 የትምህርት ዘመን ክልላዊ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ናጋሽ ዋጌሾ÷በትምህርት የታነጸ እና እውቀት የተገነባ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርቱን ተግባር በቅንጅት መምራት ይጠበቃል ብለዋል።
ያለበቂ ዕውቀት የሚመሩ ተግባራት በቂና አስተማማኝ ውጤት አያስመዘግቡም ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ለዚህም የትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አጽንኦተት ሰጥተዋል፡፡
ዶክተር ነጋሽ ስራው ውስብስብ ሂደቶችን የሚያልፍ እንደመሆኑ የትምህርት ልማት ስራዎች በዘርፉ ዕውቀት እና ልምድ ባካበቱ አመራሮች መመራት አለበት ብለዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው÷የሀገሪቱን ሁለንታናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ትምህርት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሴክተሩ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮቸን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት በመስጠት ሊደግፉ ይገባል ብለዋል።
በ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ በክልሉ አዲሱ የፍኖታ ካርታ ተግባራዊ በማድረግ እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.