Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ባለፈው አንድ ወር ብቻ 31 ሺህ 449 ጥይት እና 47 ክላሽ መያዙን ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ባለፈው አንድ ወር ብቻ 31 ሺህ 449 የተለያዩ ጥይቶች፣ 47 ክላሽ እና ሽጉጦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በሰጡት መግለጫ÷የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት ለማደፍረስ የህወሓት፣ የሸኔና የአልሸባብ ኃይሎች በተለያየ መንገድ በርካታ ሙከራ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
 
የብሔርና የብዝሓነት ልዩነቶችን በመጠቀም ሁከትና ሽብር ለመፍጠር ሙከራ መኖሩን ጠቁመው÷ የአዲስ አበባን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ እያከሸፈው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
 
በመዲናዋ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በርካታ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ወደ መዲናዋ ለመግባት መሞከሩን አስታውሰዋል፡፡
 
በዚህም ባለፈው 1 ወር ብቻ 2 ሺህ 978 የብሬን ጥይት፣ 18 ሺህ 198 የሽጉጥ ጥይት፣ ከ 10 ሺህ 273 የክላሽ ጥይት፣ 47 ክላሽ እና ሽጉጦች ተይዘዋል ነው ያሉት፡፡
 
 
በተጨማሪም 54 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና ከ280 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ገንዘብ እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ የዓረብ ሪያል መያዙን ተናግረዋል፡፡
 
ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።
 
 
በዓለምሰገድ አሳየና አወል አበራ
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.