Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች ይኖሩታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ የብዝኃ ዋና ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከክልሉ ስድስቱም ዞኖች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይት መድረኩ የብዝኃ ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ቦንጋ፣ ተርጫ፣ ሚዛን አማን እና ቴፒ እኩል ደረጃ ያላቸው የክልሉ ዋና ከተሞች ይሆናሉ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡
ቦንጋ ከተማ የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ፣ ተርጫ የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ፣ ሚዛን አማን የዳኝነት አካል መቀመጫ እንዲሁም ቴፒ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ እንደሚሆኑም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።
የክልሉ ዋና ከተሞች አራት እንዲሆኑ የተደረገው ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ መሆኑም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ የሚተገበር ከሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች ያሉት የመጀመሪያው ክልል እንደሚሆን መገለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.