Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ ዜጎች እና ተቋማት ከ253 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በጦርነት ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ተቋማት በተለያዩ የልማት ድርጅቶች ከ253 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረጓል፡፡
የገንዘብ ድጋፉ “ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ” የተሰኘው ድርጅት ከስምንት ሀገር በቀል የልማት ድርጅቶች ጋር በመተባበር የለገሱት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የተደረገው ድጋፍ በጦርነት ለተጎዱ እና ለተለያዩ ችግርች ተጋላጭ ለሆኑ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ልዩ ልዩ ተቋማት የሚውል ነው ተብሏል።
ድጋፉ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶችን ጨምሮ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 32 ትምህርት ቤቶች፣ 17 ጤና የተቋማት እና የግብርና ቢሮዎችን መልሶ ለማቋቋም እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት በክልሉ 288 ቢሊየን ብር የሚገመት ውድመትእንደደረሰ በጥናት መረጋገጡይታወሳል፡፡

አሁን ላይም በአማራ ክልል ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ጨምሮ 8 ነጥብ 7 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎች እርዳታ እንደሚሹ ተጠቁሟል፡፡
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.