Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል በአንድ ጀምበር 25 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በአራተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ በአንድ ጀምበር 25 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ÷ በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ መስፍን ቃሬ እንደገለጹት÷ የደን መጨፍጨፍ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ የአካባቢ ጥበቃና የችግኝ ተከላ ሥራዎችን ማከናወን ይገባል፡፡
በዛሬው ዕለት 25 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸው÷ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት የሚውሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በክልሉ በሚገኙ በሁሉም አካባቢዎች እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው፣ አፈወርቅ ዓለሙ እና ታመነ አረጋ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.