Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ግዳጅ ቀጠና ተልዕኮውን እየፈፀመ ያለው የሠራዊት ክፍል የሚቃጡ ትንኮሳዎችን መመከት የሚያስችል አስተማማኝ ዝግጁነት መፍጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ግዳጅ ቀጠና ተልዕኮውን እየፈፀመ ያለው የሠራዊት ክፍል ከውስጥም ይሁን ከውጭ በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ ትንኮሳዎችን መመከትና መቀልበስ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አስተማማኝ ዝግጁነት መፍጠሩን የዕዙ ምክትል አዛዥ ተናገሩ።
ጀነራል መኮንኑ እንደገለጹት÷በአውደ ውጊያ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በየ ደረጃው ያለ አመራር ቅንጅት፣ ቁርጠኝነትና ጠንካራ አመራር ሰጪ መሆን የማይተካ ሚና አለው፡፡
ጠላት ሀገርና ሕዝብን ሊያዋርድ አቅሙን አሟጦ ሲፍጨረጨር በመጠንከራችን ጠላትን ከፍላጎቱ በታች ማድረግ ችለናል ያሉት ምክት አዛዡ÷ በዚህ ሂደት በየ ደረጃው ያለ አመራር ሚና የማይተካ እንደነበር በመጥቀስ አመራሮች አቅማቸውን በቀጣይነት አዳብረው የክፍሎቻቸውን አቅም በማሳደግ ለተሻለ ግዳጅ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አመራሮች የሚመሩትን ሠራዊት የማድረግ አቅምና የዝግጁነት ደረጃ ለማሳደግ የሚያግዙ የመሪነት ክህሎትን የሚያዳብሩ ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸው ማመላከታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.