Fana: At a Speed of Life!

አቶ አወል አርባ የአዋሽ ወንዝ ሙላት ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በአዋሽ ወንዝ መሙላት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል በአይሳኢታ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎበኙ፡፡
 
አቶ አወል አርባ የአዋሽ ወንዝ በየዓመቱ ከመጠን በላይ በመሙላት ሳቢያ በተፋሰሱ በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትል አስታውሰዋል፡፡
 
አዋሽ ወንዝ ቀደም ባሉት ዓመታት በተደጋጋሚ ጊዜያት በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላት በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በቁም እንስሳት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል፡፡
 
በተያዘው የክረምት ወቅት የወንዙን መሙላት ተከትሎ ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አዳጋ ለመቀነስም በተፋሰሱ አካባቢዎች የቅድመ ዝግጀት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
 
በተፋሰሱ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችም በወንዙ ከመጠን በላይ መሙላት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን የጎርፍ አደጋ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚሰራው ስራ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
 
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ግብርና ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.